Ethiopia TV +

የቀጥታ ስርጭት, ፊልሞች እና ሙዚቃ

ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : ስለ አምላክ መኖር እና የሃይማኖት ልዩነት

ከፀሎት በኋላም ስራ ስለሌለኝ ሁልጊዜ ስለሰዎች ክፋትና ሰዎች በእርሱ ስም ሲበድሉ፣ ወንድሞቻቸውን ጉዋደኖቻቸውን ሲያባርሩ እና ሲገድሉ ዝም በማለቱ ስለፈጣሪ ጥበብ አስብ ነበር፡፡ በዚህም ጊዜ ፈረንጆቹ አየሉ፡፡ ነገር ግን ያገሩ ሰዎችም ከነሱ የባሰ ክፋት ሰሩ እንጅ ፈረንጆቹ ብቻቸውን አልነበረም የከፉት፡፡ የካቶሊክ ሃይማኖት የተቀበሉት ኦርቶዶክሶች 3 የመንበረ ጴጥሮስን እውነተኛዋን ሃይማኖት ክደዋልና የእግዚያብሔር ጠላቶች ናቸው አሉ፡፡ ስለዚህም አሳደዱአቸው፡፡ ኦርቶዶክሶችም ለሃይማኖታቸው እንዲሁ አደረጉ፡፡ እግዚያብሔር የሰዎች ጠባቂ ከሆነ ለምን ፍጥረታቸው እንዲህ ከፋ ብየ አሰብኩ፡፡ በአርያም የሚያውቅ አለን ? ኧረ እግዚያብሔርስ ያውቃልን ? በቅዱስ ስሙ ሲበድሉና ሲረክሱ የሚያውቅ ከሆነ እንዴት የሰዎችን ክፋት ዝም ይላል? አልኩ፡፡ ምንም ልብ አላደረኩም ብዙ አሰብኩ፡፡ የፈጠርከኝ ፈጣሪየ ሆይ አዋቂ አድርገኝ፤ የተደበቀውን ጥበብህን ንገረኝ ብየ ፀለይኩ፡፡ ለሙት እንዳይተኙ አይኖችህን አብራቸው እጆችህ አደረጉኝና ሰሩኝ፡፡ ትዕዛዝህን እንድማር ልብ ስጠኝ፡፡ ለኔ ግን እግሮቼ በተፍገመገሙ፤ ተረከዞቸም በተንሸራተቱ ነበር ፡፡ ይህም በፊቴ ስላለው ድካም ነው፡፡ ይህንን እና ይህን የመሰለ ፀሎት አደርግ ነበር፡፡ አንድ ቀን እኔ ወደ ማን ነው የምፀልየው አልኩ፡፡ በእውነት የሚሰማኝ እግዚያብሔር አለን? በዚህም አሳብ በጣም አዝኜ እንዲህ አልኩ ፡፡ ዳዊት እንዳለ እንዴት ምንኛ ልቤን አፀደኳት፡፡ ኋላም አሰብኩ ይህ ዳዊት እንዲህ የሚለው ጆሮን የተከለ አይሰማምን ? በእውነት እንድሰማበት ጆሮ የሰጠኝ ማነው? አዋቂስ አድርጎ የፈጠረኝ ማነው? በዚህስ አለም እኔ እንደምን መጣሁ? ከዓለም በፊት ብኖር የህይወቴ መጀመሪያና የእውቀቴ መጀመሪያን ባወኩ፡፡ እኔ በገዛ እጄ ተፈጠርኩን ? ነገር ግን እኔ በተፈጠርኩ ጊዜ አልኖርኩም፡፡ አባት እናቴ ፈጠሩኝ ብልም እንደገና ወላጆችና የወላጆችን ወላጅ፣ወላጅ የሌላቸው በሌላ መንገድ ወደዚህ ዓለም የመጡትን እንደኛ ያልተወለዱትን የፊተኞቹ ድረስ ፈጣሪያቸውን እፈልጋለሁ፡፡ እነርሱም ቢወለዱ የፈጠራቸው አንድ ህላዌ አለ ከማለት በቀር የጥንት መወለጃቸውን አላውቅም፡፡ ያለና በሁሉም የሚኖር የሁሉ ጌታ ሁሉን የያዘ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ዓመቱ እማይቆጠር እማይለወጥ ያልተፈጠረ ፈጣሪ አለ አልኩ፡፡ ፈጣሪስ አለ፡፡ ፈጣሪ ባይኖር ፍጥረት ባልተገኘ አልኩ፡፡ እኛ ብንኖር ፍጡራን እንጅ ፈጣሪዎች አይደለንም፡፡ የፈጠረ ፈጣሪ አለ እንል ዘንድ ይገባናል፡፡ ይህም የፈጠረን ፈጣሪ አዋቂና ተናጋሪ ካልሆነ በቀር ከዕውቀቱ በተረፈ አዋቆዎችና ተናጋሪዎች አድርጎ ፈጥሮናል፡፡ ሁሉን ፈጥሯል ሁሉን ይይዛልና እርሱ ሁሉን ያውቃል፡፡ ፈጣሪየ ወደ እርሱ ስፀልይ ይሰማኛል ብየ ሳስብ ትልቅ ደስታ ተደሰትኩ፡፡ በትልቅ ተስፋም እየፀለይኩ ፈጣሪየን በሙሉ ልቤ ወደድኩት፡፡ ጌታየ ሆይ አንተ ሃሳቤን ሁሉ ከሩቅ ታውቃለህ አልኩት፡፡ አንተ የመጀመሪያየ ነህ፡፡ የመጨረሻየን ሁሉን አወቅህ፡፡ መንገዴንም ሁሉ አንተ አስቀድመህ አወቅህ፡፡ ስለዚህም ከሩቅ ታውቃለህ ይሉሃል፡፡ እኔ ሳልፈጠር ሀሳቤን ያውቃልና ፈጣሪየ ሆይ እውቀትን ስጠኝ አልኩ፡፡  

ተዛማጅ ልጥፎች:

  • ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : በሃይማኖት ስለመጣው መቅሰፍትና የፋሲለደስ ታሪክ በ 1635 ዓ/ም በህዝብ ሃጢያት እና ፍቅረቢስነት ፍቅር ማጣት በኢትዮጵያ ሁሉ ትልቅ እረሃብ ብርቱ መቅሰፍት ሆነ፡፡ ንጉስ ሱስንዮስና የአቦነ አልፎንዝን ሃይማኖት የተቀበሉ ሃይማኖታቸውን ያልተቀበሉ ወንድሞቻቸውን መጀመሪያ ገደሉ፣ አባረሩ፡፡ የተሰደዱትም በኋላ ከጠላቶቻቸው ብዙዎቹን ገደሉና አፀፋ መለሱ፡፡ በኋላቸውም ሆነ በፊታቸው የእግዚያብሔር ፍርሀት … ተጨማሪ ያንብቡ
  • ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : የዘርዓ ያዕቆብ ወደ እንፍራንዝ መግባት በ1625 ዓ/ም ሱስንዮስ ሞቶ ልጁ ፋሲለደስ ነገሰ፡፡ እርሱም በመጀመሪያ ፈረንጆቹን ወደደ፡፡ ግብፃዊያንንም አላባረራቸውም በዚህ ምክንያት በኢትዮጵያ ሁሉ ሰላም ሆነ፡፡ የዚያን ጊዜ ከዋሻየ ወጥቼ መጀመሪያ ወደ አማራ አገሮች ሄድኩ፡፡ ኋላም ወደ በጌምድር ተመለስኩ ለሁሉም በፈረንጆች ጠላትነት በሱስንዮስ ዘመን ከተባረሩት መነኮሳት አንዱ መሰልኳቸው ፡፡ ስ… ተጨማሪ ያንብቡ
  • ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : ስለ ባህሪያዊ ዕውቀት የፈጣሪ ፈቃድ ግን ለእግዚያብሔር ለፈጣሪ ስገድ ፣ ሰውንም ሁሉ እንደነፍስህ አፍቅር ይላል፡፡ ይህ በልቦናችን እውነት መሆኑ ይታወቃል፡፡ እንደገናም በልቦናችን እውነትነቱ የሚታወቅ ሌላ እውነት "ሊያደርጉብህ የማትፈልገውን በሰው አታድርግ፡፡ ላንተ ሊያደርጉልህ የምትፈልገውን አድርግላቸው" ይላል፡፡ የሰንበትን ማክበር የሚለው ካልሆነ በቀር አስሩ የኦሪት ት… ተጨማሪ ያንብቡ
  • ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : ስለ ሕጋዊ የፈቃድ ጋብቻ ይህ መንገድ ወደ አበሳ ይስባልና ሴት የሌላቸው ወንድ ብቻውን ይኖር ዘንድ እንደማይገባው አወኩ፡፡ ለፊተኞቹ ሴት ታስፈልጋቸዋለች እንጅ ወንድ ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም፣ እንደተባለው በሰሩት ወጥመዳቸው እንዳይጠመዱ ሰዎች ተፈጥሯቸውን ክደው ሊኖሩ አይገባቸውም፡፡ ጌታየ ሀብቱም የዘመኑን ክፋት ፈርቼ መሰልኩ እንጂ መነኩሴ አይደለሁም አልኩት፡፡ … ተጨማሪ ያንብቡ
  • ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : ስለ ፈተናና ፀሎት እኔም እነደገና በሙሉ ልባችን በፍቅርና በዕምነት በትዕግስትም ወደ እርሱ በፀለይን ጊዜ እግዚያብሔርም ፀሎታችንን እነደሚሰማ በሌላ መንገድ አወኩ፡፡ እኔ በልጅነት ጊዜየ ስለ እግዚያብሔር ሥራ ምንም ሳላስብ ወደ እርሱ ስፀልይ ሃጢያተኛ ነበርኩ፡ ፡ለአዋቂ ፍጥረት የማይገባ ብዙ በደል በደልኩ፡፡ ስለሃጢያቴም ሰው ከእርሱ ሊያመልጥ ወደማይችለው ወጥመድም ወደኩ… ተጨማሪ ያንብቡ

ታዋቂ ልጥፎች

እኛ ተከታታይ ፊልሞችን እና በርካታ የተጨመረ ነጻ ይዘት ወይም የደንበኝነት ምዝገባን የሚያቀርብ ጣቢያ ነው, በእርግጥ በቀጥታ እና በቀጥታ ለመመልከት እና ጥራት ያላቸውን የጥራት ደረጃ ይዘት ለማቅረብ በምናደርጋቸው ጥረቶች እና በጥራት ላይ አናመክርም. የምንሰግበው ነጻ የዥረት አገልግሎት ከሚሰጠን በስተቀር, ተከታታይ ፊልሞችን እና ፊልሞችን ወደ ኮምፒውተርዎ ማውረድ ይችላሉ, ቆይተው ለማየት እንዲያደርጉዋቸው, ለምሳሌ የበይነመረብ ግንኙነት ከሌለዎት. በቀጥታ ወደ ፊልሞች ከመሄድ የተሻለ ይሆናል, ሁሌም አስር ኪሎ ግራም ለ 2 ሰዓታት ፊልም አንፈልግም ማለት ነው, ስለዚህ ጣቢያዎቻችን ለቀኝ እይታ እና ተከታታይ ፊልሞችን ያቀርባሉ, ይህም አንድ ጊዜ ጠቅ በማድረግ ይዘትዎን በጥሩ ጥራት ለመመልከት ያስችልዎታል. እንዲሁም በቴሌቪዥን ወይም በሌሎች የዥረት አገልግሎት ላይ ለሚደረግ ማንኛውም ምርመራ የተመረጠውን በይነመረብ በቀጥታ መመልከት ይመርጣል. አብዛኛዎቹ እነዚህ አገልግሎቶች የሚከፈልባቸው ወይም ጥራት የሌላቸው ናቸው. ጊዜን እና አላስፈላጊዎቹን ፍለጋዎች ለመቆጠብ, በጣም ደጋግመው ጣቢያውን እናምናለን, ስለዚህ አብዛኛዎቹ ፊልሞች እና ተከታታይ ፊልሞች ቅድመ እይታ ወደ መጀመሪያ ጣቢያችን ይሄድና ከሌሎች ጣቢያዎች በበለጠ ፍጥነት ይሻሻላሉ. ከተለቀቀው ፊልም ወይም ተከታታይ ጋር በጣቢያው ላይ በቋሚነት ለመመልከት ሁሉም ፊልሞች እና ተከታታይ ፊልም ቅድመ-ኮድ ውስጥ ይቀመጣሉ, ስለዚህ ስራዎን ለእርስዎ እየሠራን ስለሆነ በድር ላይ ትርጉሞችን መፈለግ የለብዎትም. የመስመር ላይ ፊልሞች እና ፊልሞች የእርስዎ አዲሱ ፊልም ነው.