Ethiopia TV +

የቀጥታ ስርጭት, ፊልሞች እና ሙዚቃ

ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : ስለ ሃይማኖቶች መለየት

ሌላ ትልቅ ምርመራ አለ፡፡ ሰዎች ሁሉ በእግዚያብሔር ዘንድ ትክክል ናቸው፡፡ እርሱም አንድ ህዝብ ለሕይወት አንድ ህዝብ ለሞት አንድም ለምህረት አንድም ለኩነኔ አልፈጠረም፡፡ ይህም አድሎ በስራው ሁሉ ፃድቅ በሆነ በእግዚያብሔር ዘንድ እንደማይገኝ ልቦናችን ያስተምረናል፡፡ ሙሴ ግን አይሁድን ለብቻቸው እንዲያስተምራቸው ተላከ፡፡ ለሌሎች ሕዝቦች ፍርዱ አልተነገረም፡፡ እግዚያብሔር ስለምን ለአንድ ህዝብ ፍርድ ሲነግር ለሌላው አልነገረም፡፡ በዚህ ጊዜ ክርስቲያኖች የእግዚያብሔር ትምህርት ከኛ ጋር ካልሆነ በስተቀር አይገኝም ይላሉ፡፡ አይሁድና እስላም የህንድ ሰዎችም ሌሎችም ሁሉ እንደነሱ ይላሉ፡፡ እንዲሁ ደግሞ ክርስቲያኖች እርስ በርሳቸው አይስማሙም፡፡ ካቶሊኮች እግዚያብሔር ከኛ ጋር ነው ያለ እንጂ ከናንተ ጋር አይደለም ይሉናል፡፡ እኛም እንዲሁ እንላለን፡፡ ሰዎች እንደምንሰማቸው ግን የእግዚያብሔር ትምህርት እጅግ ጥቂቶች ወደሆኑት እንጂ ለብዙዎቹ አልደረሰም፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ደግሞ ወደ ማን እንደደረሰ አናውቅም፡፡ እግዚያብሔር ከፈቀደ ቃሉን በሰው ዘንድ ማፅናት ተስኖት ነውን? ሆነም ግን የእግዚያብሔር ጥበብ በመልካም ምክር ይህ ነገር እውነት እንዳይመስላቸው ሰዎች በሐሰት ሊስማሙ አልተወም፡፡ ሰዎች ሁሉ በአንድ ነገር በተስማሙ ጊዜ ይህ ነገር እውነት ይመስላል፡፡ ሰዎች ሁሉ በሃይማኖታቸው ምንም እንደማይስማሙ በሃሳብም ሊስማሙ አይችሉም፡፡ እስኪ እናስብ ሰዎች ሁሉ ሁሉን የፈጠረ እግዚያብሔር አለ በማለታቸው ስለምን ይስማማሉ? ፍጡር አለ ፈጣሪ ሊገኝ እንደማይችል፤ ስለዚህም ፈጣሪ እንዳለ እውነት ነውና ነው፡፡ ይህ የምናየው ሁሉ ፍጡር እንደሆነ የሰው ሁሉ ልቦና ያውቃል ፡፡ ሰዎች ሁሉ በዚህ ይስማማሉ፡፡ ነገር ግን ሰዎች ያስተማሩትን ሃይማኖት በመረመርን ጊዜ በውስጡ ሐሰት ከእውነት ጋር ተቀላቅሎበታል፡፡ ስለዚህ እርስ በርሱ አይስማማም፡፡ ሰዎች እርስ በርሳቸው አንዱ ይህ እውነት ነው ሲል፡፡ ሁለተኛው አይደለም ሐሰት ነው ሲል ይጣላሉ፡፡ ሁሉም የእግዚያብሔርን ቃል የሰው ቃል እያደረጉ ይዋሻሉ፡፡ እንደገናም የሰው ሃይማኖት ከእግዚያብሔር ብትሆን ክፉዎችን ክፉ እንዲያደርጉ እያስፈራራች መልካም እንዳያደርጉ ትፈቅድላቸው ነበር፡፡ ደጎችንም በትዕግስታቸው ታፀናቸው ነበር፡፡ ለኔም እንዲህ ያለው ሃይማኖት ባሏ ሳያውቅ በምንዝርና 9 የወለደች ሴትን ትመስለኛለች፡፡ ባሏ ግን ስለመሰለው በሕፃኑ ይደሰታል፡፡ እናቲቱንም ይወዳታል፡፡ በዝሙት እንደወለደችው ባወቀ ጊዜ ግን ያዝናል፡፡ ሚስቱንም ልጅዋንም ያባርራል፡፡ እንዲሁም እኔም ሀይማኖቴን አመንዝራና ዋሾ መሆኑዋን ካወኩ በኋላ ስለርሷ በዝሙት ስለተወለዱ ልጆቿ አዘንኩ ፡፡ እነሱ በጠብ፣ በማሳደድ፣ በመማታት፣ በማሰር፣ በመግደል ወደዚህ ዋሻ ያባረሩኝ ናቸው፡፡ ነገር ግን የክርስቲያን ሃይማኖት እውነት ናት እንዳልል በዘመነ ወንጌል እንደተሰራ ክፉ አልሆነችም፡፡ የምህረትን ሥራ በሙሉ እርስ በርስ መፋቀርን ታዛለች፡፡ በዚህ ዘመን ግን የሀገራችን ሰዎች የወንጌልን ፍቅር ወደ ጠብና ሃይል ወደ ምድራዊ መርዝ ለወጡት፡፡ ሃይማኖታቸውን ከመሰረቱ አመፃ እየሰሩ ከንቱ ያስተምራሉ፡፡ በሐሰትም ክርስቲያኖች ይባላሉ፡፡ 

ተዛማጅ ልጥፎች:

  • ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : የዘርዓ ያዕቆብ የፍፃሜ ታሪክ ልጄም አድጎ ያማረ ጎበዝ ሆነ፡፡ ሃያ ዓመትም በሆነ ጊዜ እርሱ ባለማወቅ ወደ ምንኩስና እናዳዘነበለ አወቅሁ፡፡ "ይህ ስራ ፈጣሪ ለኛ የሰራልንን ሥርዓት ያፈርሳልና አይገባም" ብየ ብዙ ተቆጣሁት፡፡ "ነገር ግን በተፈጥሯችን ስርዓት ሚስት አግብተህ ኑር" አልኩት፡፡ "እሺ ሚስት ስጠኝ" አለኝ፡፡ ላምጌ ከተባለው አገር መድሃኒት የተባለች የአርብቶ አደሮችን … ተጨማሪ ያንብቡ
  • ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : በሃይማኖት ስለመጣው መቅሰፍትና የፋሲለደስ ታሪክ በ 1635 ዓ/ም በህዝብ ሃጢያት እና ፍቅረቢስነት ፍቅር ማጣት በኢትዮጵያ ሁሉ ትልቅ እረሃብ ብርቱ መቅሰፍት ሆነ፡፡ ንጉስ ሱስንዮስና የአቦነ አልፎንዝን ሃይማኖት የተቀበሉ ሃይማኖታቸውን ያልተቀበሉ ወንድሞቻቸውን መጀመሪያ ገደሉ፣ አባረሩ፡፡ የተሰደዱትም በኋላ ከጠላቶቻቸው ብዙዎቹን ገደሉና አፀፋ መለሱ፡፡ በኋላቸውም ሆነ በፊታቸው የእግዚያብሔር ፍርሀት … ተጨማሪ ያንብቡ
  • ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : ስለ ጌታየ ሀብቱ ሞትና የልጁ ታሪክ ካንድ አመት በኋላ ጌታየ ሀብቱ ሞተብንና እጅግ አዘንን፡፡ ትልቅ ለቅሶ አለቀስን እሱ ሳይሞት ጠርቶ ይኸው እኔ እሞታለሁ እግዚያብሔር ይጠብቃችሁ ይባርካችሁና አንተም ለልጆቼ አባት ሁናቸው አለኝ፡፡ አንድ በሬና አንድ በቅሎም ሰጠኝ፡፡ ለሚስቴም ሁለት ላሞች ከነልጆቿ ሰጣት፡፡ ስለነፍሴ ፀልዩ ብሎን በእግዚያብሔር ሰላም ሞተ፡፡ እርሱ በተባረከች ነፍሱ አረፈ… ተጨማሪ ያንብቡ
  • ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : ስለ ሕጋዊ የፈቃድ ጋብቻ ይህ መንገድ ወደ አበሳ ይስባልና ሴት የሌላቸው ወንድ ብቻውን ይኖር ዘንድ እንደማይገባው አወኩ፡፡ ለፊተኞቹ ሴት ታስፈልጋቸዋለች እንጅ ወንድ ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም፣ እንደተባለው በሰሩት ወጥመዳቸው እንዳይጠመዱ ሰዎች ተፈጥሯቸውን ክደው ሊኖሩ አይገባቸውም፡፡ ጌታየ ሀብቱም የዘመኑን ክፋት ፈርቼ መሰልኩ እንጂ መነኩሴ አይደለሁም አልኩት፡፡ … ተጨማሪ ያንብቡ
  • ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ መግቢያ እግዚያብሔርን የምትፈሩ ሁሉ ለነፍስ ያደረጋችሁትን መናገር እጀምራለሁና ኑ ስሙኝ፡፡ ሁሉን በፈጠረ መጀመሪያና መጨረሻ በሆነ ሁሉን በያዘና የህይወትና የጥበብ ሁሉ ምንጭ በሆነ እግዚያብሔር በሰጠኝ ረዥም እድሜየ ትንሽ እፅፋለው፡፡ ነፍሴ በእግዚያብሔር ዘንድ የተከበረች ትሁን ጆሮዎችም ሰምተው ይደሰቱ፡፡ እኔ እግዚያብሔርን ፈለኩት መለሰልኝ፡፡ አሁንም እናን… ተጨማሪ ያንብቡ

ታዋቂ ልጥፎች

እኛ ተከታታይ ፊልሞችን እና በርካታ የተጨመረ ነጻ ይዘት ወይም የደንበኝነት ምዝገባን የሚያቀርብ ጣቢያ ነው, በእርግጥ በቀጥታ እና በቀጥታ ለመመልከት እና ጥራት ያላቸውን የጥራት ደረጃ ይዘት ለማቅረብ በምናደርጋቸው ጥረቶች እና በጥራት ላይ አናመክርም. የምንሰግበው ነጻ የዥረት አገልግሎት ከሚሰጠን በስተቀር, ተከታታይ ፊልሞችን እና ፊልሞችን ወደ ኮምፒውተርዎ ማውረድ ይችላሉ, ቆይተው ለማየት እንዲያደርጉዋቸው, ለምሳሌ የበይነመረብ ግንኙነት ከሌለዎት. በቀጥታ ወደ ፊልሞች ከመሄድ የተሻለ ይሆናል, ሁሌም አስር ኪሎ ግራም ለ 2 ሰዓታት ፊልም አንፈልግም ማለት ነው, ስለዚህ ጣቢያዎቻችን ለቀኝ እይታ እና ተከታታይ ፊልሞችን ያቀርባሉ, ይህም አንድ ጊዜ ጠቅ በማድረግ ይዘትዎን በጥሩ ጥራት ለመመልከት ያስችልዎታል. እንዲሁም በቴሌቪዥን ወይም በሌሎች የዥረት አገልግሎት ላይ ለሚደረግ ማንኛውም ምርመራ የተመረጠውን በይነመረብ በቀጥታ መመልከት ይመርጣል. አብዛኛዎቹ እነዚህ አገልግሎቶች የሚከፈልባቸው ወይም ጥራት የሌላቸው ናቸው. ጊዜን እና አላስፈላጊዎቹን ፍለጋዎች ለመቆጠብ, በጣም ደጋግመው ጣቢያውን እናምናለን, ስለዚህ አብዛኛዎቹ ፊልሞች እና ተከታታይ ፊልሞች ቅድመ እይታ ወደ መጀመሪያ ጣቢያችን ይሄድና ከሌሎች ጣቢያዎች በበለጠ ፍጥነት ይሻሻላሉ. ከተለቀቀው ፊልም ወይም ተከታታይ ጋር በጣቢያው ላይ በቋሚነት ለመመልከት ሁሉም ፊልሞች እና ተከታታይ ፊልም ቅድመ-ኮድ ውስጥ ይቀመጣሉ, ስለዚህ ስራዎን ለእርስዎ እየሠራን ስለሆነ በድር ላይ ትርጉሞችን መፈለግ የለብዎትም. የመስመር ላይ ፊልሞች እና ፊልሞች የእርስዎ አዲሱ ፊልም ነው.