ለሚመረምር ግን እውነት ቶሎ ይገለፃል፡፡ ፈጣሪ በሰው ልብ ያስገባውን ንፁህ ልቦና የፍጥረት ሕግጋትና ስርዓትን
ተመልክቶ የሚመረምር እርሱ እውነትን ያገኝል፡፡ ሙሴ ፈቃዱንና ሕጉን ልነግራችሁ ከእግዚያብሔር ዘንድ ተልኬ መጣሁ ይላል፡፡ ከርሱ በኋላ የመጡት በግብፅና በደብረሲና እንዲህ ተደረገ እያሉ ታሪክን፣ ተዓምራትን እየጨመሩ የሙሴን ነገር
እውነት አስመሰሉት፡፡
የሙሴ መፅሃፍ ከፍጥረት ሕግ ሰርዓትና ከፈጣሪ ጥበብ ጋር አይስማማም፡፡ ከውስጡ የተሳሳተ ጥበብ ይገኛል፡፡
ለሚመረምር ግን እውነት አይመስለውም፡፡ በፈጣሪ ፈቃድና በፍጥረት ህግ የሰው ልጅ እንዳይጠፋ ልጆችን ለመውለድ
ወንድና ሴት በፍትወተ ስጋ እንዲገናኙ ታዟል፡፡ ይህም ግንኙነት እግዚያብሔር ለሰው በሕገ ተፈጥሮ የሰጠው ነው፡፡
እግዚያብሔርም የእጁን ስራ አያረክስም፡፡ እግዚያብሔር ዘንድ እርኩሰት ሊገኝ አይችልም፡፡ ሙሴ ይህን ማለቱ ትክክል ነው
አልልም፡፡ ፈጣሪውን ዋሾ እንዳደረገው ልቦናችን ያስረዳናል፡፡ እንደገናም የክርስቲያን ሕግ ለማስረጃዋ ተአምራቶች
ተገኝተዋልና ከእግዚያብሔር ናት ይላሉ፡፡ ነገር ግን የወሲብ ስርዓት የተፈጥሮ ስርዓት እንደሆነ ምንኩስና ግን ልጆች
ከመውለድ ከልክሎ የሰውን ፍጥረት አጥፍቶ የፈጣሪን ጥበብ የሚያጠፋ እነደሆነ ልቦናችን ይነግረናልና ያስረዳናል፡፡
የክርስቲያን ሕግ ምንኩስና ከወሲብ ይበልጣል ብትል ሐሰት ትናገራለችና ከእግዚያብሔር አይደለችም፡፡ የፈጣሪን ሕግ
የሚያፈርስ እንዴት ከጥበብ በለጠ ? ወይስ የእግዚያብሔርን ስራ የሰው ምስክር ሊያስተካክለው ይቻለዋልን ?
እንዲሁም መሐመድ የማዛችሁ ከእግዚያብሔር የተቀበልኩትን ነው ይላል፡፡ መሐመድን መቀበል የሚያስረዱ ተዓምራት
ፀሐፊዎች አልጠፉምና ከሱም አመኑ፡፡ እኛ ግን የመሐመድ ትምህርት ከእግዚያብሔር ሊሆን እንደማይችል እናውቃለን፡፡
የሚወለዱ ሰዎች ወንድና ሴት ቁጥራቸው ትክክል ነው፡፡ በአንድ ሰፊ ቦታ የሚኖሩ ወንድ ሴት ብንቆጥር ለእያንዳንዱ ወንድ
አንዲት ሴት ትገኛለች እንጂ ለአንድ ወንድ ስምንት ወይም አስር ሴቶች አይገኙም፡፡ የተፈጥሮ ህግም አንዱ ከአንዲት ጋር
እንዲጋቡ አዟል፡፡ አንድ ወንድ አስር ሴት ቢያገባ ግን ዘጠኝ ወንዶች ሴት የሌላቸው ይቀራሉ፡፡ ይህም የፈጣሪን ስርዓትና
ሕገ ተፈጥሮን የጋብቻንም ጥቅም ያጠፋል፡፡ አንድ ወንድ ብዙ ሴቶች ሊያገባ ይገባዋል ብሎ በእግዚያብሔር ስም ያስተማረ
መሐመድ ግን ትክክል ነው አልልም፡፡ ከእግዚያብሔር ዘንድ አልተላከም፡፡
ጥቂት ስለጋብቻ ሕግ መረመርኩ ፡፡ የቀረውን ብመረምርም በህገ ኦሪትና በክርስትና በእስልምና ሕግ ፈጣሪ በልቦናችን
ከሚገልፅልን እውነት እና እምነት አይስማማም፡፡ ብዙ አይገኝበትም አልኩ፡፡ ፈጣሪ ለሰው ልጅ ክፉና መልካም የሚለይበት
ልቦና ሰጥቶታል፡፡ በብርሀን ብርሀን እናያለን እንደተባለውም የሚገባውን የማይገባውን ሊያውቅ፣ እውነትን ከሐሰት
እንዲለይ ነው፡፡ ስለዚህ የልቦናችን ብርሀን እንደሚገባ በእርሱ ብናይበት ሊታይልን አይችልም፡፡ ፈጣሪያችን ይሄን ብርሃን
የሰጠን በርሱ እንድንድን ነው እንጅ እንድንጠፋ አይደለም፡፡የልቦናችን ብርሀን የሚያሳየን ሁሉም ከእውነት ምንጭ ነው፡፡
ሰዎች ከሐሰት ምንጭ ነው ቢሉን ግን ሁሉን የሰራ ፈጣሪ ቅን እንደሆነ ልቦናችን ያስረዳናል፡፡ ፈጣሪ በመልካም ጥበቡ
ከሴት ልጅ ማህፀን በየወሩ ደም እንዲፈስ አዟል፡፡ ሙሴና ክርስቲኖች ግን ይህን የፈጣሪ ጥበብ እርኩስ አደረጉት፡፡ እንደገና ሙሴ እንዲህ ያለችውን ሴት የተገናኛት ያረክሳል፡፡ ይህም የሙሴ ህግ የሴትን ኑሮ በሙሉና ጋብቻዋን ከባድ
አድርጎታል፡፡ የመራባትንም ህግ አጥፍቷል፡፡ ልጆችንም ከማሳደግ ከልክሎ ፍቅርንም ያፈርሳል፡፡ ስለዚህ ይህ የሙሴ ሕግ
ሴትን ከፈጠረ ሊሆን አይችልም፡፡ እንደገናም የሞቱትን ወንድሞቻችንን ልንቀብራቸው ተገቢ መሆኑን ልቦናችን ይነግረናል፡፡
በድኖቻቸውም በሙሴ ጥበብ ካልሆነ በስተቀር ከመሬት የተፈጠርንበት ወደመሬትም ልንገባባዘዘን በፈጣሪያችን ጥበብ
እርኩሳን አይደሉም፡፡ ነገር ግን ለፍጥረት ሁሉ እንደሚገባ በትልቅ ጥበብ የሰራ እግዚያብሔር ስርዓቱን አያረክሳውም፡፡ ሰው
ግን የሐሰትን ቃል እንዲያከብር ብሎ ሊያረክሰው ይፈልጋል፡፡
እንደገና ወንጌል አባት እና እናቱን ምሽቱን እና ልጁን ያልተወ ለእግዚያብሔር የተገባ አይሆንም ይላል፡፡ ይህ መተው የሰውን
ፍጥረት ሁሉ ያጠፋል፡፡ እግዚያብሔር ግን ፍጥረቱን በማጥፋት አይደሰትም፡፡ አባትና እናትም በሽምግልናቸው ጊዜ እረዳት
አተው እንዲሞቱ መተው ትልቅ አበሳ መሆኑን ልቦናችን ያሳየናል፡፡ እግዚያብሔርም አመፃን የሚወድ አምላክ አይደለም፡፡
ልጆችን መተው ግን ከበረሃ አራዊት ይብሳሉ፡፡ ምሽቱ ስታመነዝር የሚፈታት ሁሉ የፈጣሪን ስርዓትና የተፈጥሮን ሕግ
አፍርሷል፡፡ ስለዚህም ወንጌል በዚህ ስፍራ የሚለው ከእግዚያብሔር ሊሆን አይችልም፡፡
እንደገና በእስልምና ሰው እንደ እንስሳ ሊሸጥና ሊገዛ ይገባል ይላሉ፡፡ ፈጣሪያችን እንደ ወንድሞች አስተካክሎ ከፈጠረን
ከሰዎች ፈጣሪ ይህ የእስልምና ህግ ሊወጣ አይችልም፡፡ ልቦናችን ያውቃል እነሱ ግን ደካማን ሰው የሐይለኛ ሰው ንብረት
አደረጉት፡፡ አዋቂው ፍጥረትንም ካላዋቂው እንስሳ ጋር አስተካክሎት ይህ ከእግዚያብሔር ዘንድ ሊወጣ ይችላልን ?
እንደዚሁም እግዚያብሔር የከንቱ ነገር አያዝም፡፡ ይህን ብላ፣ ይህን አትብላ፣ ዛሬ ብላ፣ ነገ አትብላ አይልም፡፡ ለክርስቲያኖች
እንደሚመስላቸውና የጾም ሕግጋት እንደሚጠብቁ ስጋን ዛሬ ብላ ነገ አትብላ አይልም፡፡ ለክርስቲያኖች እንደሚመስላቸውና
የጾም ሕግጋት እንደሚጠብቁ ስጋን ዛሬ ብላ ነገ ግን አትብላ አይልም፡፡ እስላሞችንም እግዚያብሔር ለሊት ብሉ ቀን
አትብሉ ብሎ ይሄንና የመሳሰሉትን አይላቸውም፡፡ የፍጥረታችንን ጤና የማያውክ ነገር ሁሉ ልንበላ እንደሰለጠንን ልቦናችን
ያስተምረናል አንድ የመብል ቀን አንድ የጾም ቀን ግን ጤናን ያውካል፡፡ የጾም ህግ መብላትን ለሰው ሕይወት ከፈጠረና
ልንበላቸው ከፈቀደ ፈጣሪ የወጣ አይደለም፡፡ በልተን ልናመሰግነው እንጅ በረከቱን ልናርም አይገባንም፡፡ ሕገ ፆም የስጋን
ፍትወት ለመግደል የተሰራ ነው የሚሉም ቢኖሩ ፍትወተ ስጋ ወንድ ወደ ሴት ሊሳብ ሴትም ወደ ወንድ ልትሳብ የፈጣሪ
ጥበብ ነውና እርሱ ፈጣሪ በሰራው በታወቀ ማጥፋት አይገባም እላለሁ፡፡
ፈጣሪያችን ይህን ፍትወት ለሰው ለእንስሳት ሁሉ በከንቱ አልሰጠም፡፡ ነገር ግን ለዚህ ዓለም ሕይወትና ለፍጥረት የተሰራለት
መንገድ ሁሉ መሠረቱ ሆኖ እንዲቆይ ይህ ፍትወት ለሰው ልጅ ተሰጠ፡፡ አስፈላጊያችን ልንበላ ይገባናል፡፡ በእሁድ ቀንና
8
በበዓል ቀናት በአስፈላጊው ልክ የበላ እንዳልበደለ እንዲሁ በአርብ ቀንና ከፋሲካ በፊት ባሉት ቀናት ለክቶ የሚበላ
አልበደለም፡፡ እግዚያብሔር ሰውን በሁሉ ቀንና በሁሉ ወራት ካስፈላጊ ምግብ ጋር አስተካክሎ ፈጥሮታል፡፡ አይሁድ፣
ክርስቲያንና እስላም ግን የፆምን ሕግ ባወጡ ጊዜ ይህን የእግዚያብሔር ሥራ ልብ አላሉም፡፡ እግዚያብሔር ፆምን ሰራልን
እንዳንበላም ከለከለን እያሉ ይዋሻሉ፡፡ እግዚያብሔር ፈጣሪያችን ነው፡፡ ግን የምንበላውን ምግባችንን እንድንመገበው ሰጠን
እንጂ እርሱን ልናርም አይደለም፡፡