እግዚያብሔርን የምትፈሩ ሁሉ ለነፍስ ያደረጋችሁትን መናገር እጀምራለሁና ኑ ስሙኝ፡፡ ሁሉን በፈጠረ መጀመሪያና
መጨረሻ በሆነ ሁሉን በያዘና የህይወትና የጥበብ ሁሉ ምንጭ በሆነ እግዚያብሔር በሰጠኝ ረዥም እድሜየ ትንሽ
እፅፋለው፡፡ ነፍሴ በእግዚያብሔር ዘንድ የተከበረች ትሁን ጆሮዎችም ሰምተው ይደሰቱ፡፡ እኔ እግዚያብሔርን ፈለኩት
መለሰልኝ፡፡ አሁንም እናንተ ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል ፊታችሁንም አያሳፍርም፡፡ እግዚያብሔርን ከኔ ጋር ከፍ ከፍ
አድርጉት አብረን ስሙን እናንሳ፡፡
እኔ የተወለድኩት በአክሱም በካህናት ሀገር ነው፡፡ ነግር ግን እኔ በአክሱም አውራጃ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ በነገሰ በሶስተኛው
ዓመት በ1592 ዓ/ም ከ አንድ ገበሬ ቤተሰብ ተወለድሁ፡፡ በክርስትና ጥምቀት ዘርዓ ያዕቆብ ተብየ ተሰየምኩ፡፡ ሰወች ግን
ወርቄ ይሉኛል፡፡ ካደኩ በኋላ ትምህርት እንድማር አባቴ ወደ ትምህርት ቤት ላከኝ፡፡ ዳዊትም ከደገምኩ በኋላ መምህሬ
አባቴን ይህ ህፃን ልጅህ ልቦናው የበራ በትምህርት ታጋሽ ነውና ወደ ትምህርት ቤት ብትልከው ሊቅና መምህር ይሆናል
አለው፡፡ አባቴም ይህን ሰምቶ ዜማ እንድማር ላከኝ፡፡ ሆኖም ድምጼ ሸካራ ሆኖ አላምር አለኝ፡፡ በዚህ ምክንያት ጓደኞቼ
መሳቂያና መዘባበቻ አደረጉኝ፡፡ እዛም ሶስት ወር ያህል ቆየው፡፡ ስላልተሳካልኝ ከልቤ አዘንኩ፡፡ ተነስቼ ሰዋሰውና ቅኔ
ለመማር ወደ ሌላ አስተማሪ ሄድኩ፡፡ ከጓደኞቼ ፈጥኜ እንድማርም እግዚያብሔር ጥበቡን ሰጠኝ፡፡ ይህም የመጀመሪያ
ሃዘኔን አስረሳኝ ፡፡ በጣም ተደሰትኩ፡፡ እዛም አራት አመት ቆየሁ፡፡ በነዚያ ቀኖች እግዚያብሔር ከሞት አዳነኝ፡፡ ከጓደኞቼ
ጋር ስጫወት ወደገደል ወደኩ፡፡ እግዚያብሔር በታምራቱ አዳነኝ እነጅ ፈፅሞ ልድን አልችልም ነበር፡፡ ከዳንኩ በኋላ ገደሉን
በረዥም ገመድ ለካሁት፡፡ አስራ ሶስት ሜትር ሆኖ ተገኝ፡፡ እኔም ድኜ ያዳነኝን እግዚያብሔርን እያመሰገንኩ ወደ መምህሬ
ቤት ሄድኩ፡፡ ከዚያም ተነስቼ የቅዱሳት መፅሃፍትን ትርጉዋሜ ለመማር ሄድኩ፡፡ በዚያም አስር ዓመት ቆየሁ፡፡ መፅሃፍትን
ፈረንጆች እንዴት እነደሚተረጉሟቸው የኛም ምሁራን እንዴት እነደሚተረጉሟቸው ተማረኩ፡፡ ትርጉዋሜያቸው ግን ከኔ
ልቦና ጋር የሚስማማ አልነበረም፡፡ ሆኖም ይህን ስሜቴን ሃሳቤን ለማንም ሳልገልፅ በልቤ ይዥው ቆየሁ፡፡ ከዚያም
ወደሃገሬ ወደ አክሱም ተመለስኩ፡፡ በአክሱም ለ አራት አመት መፅሃፍ አስተማረኩ፡፡ ይህ ዘመን ክፉ ዘመን ሆነ፡፡ አፄ
ሱስንዮስ በነገሰ በ 19ኛው ዓመት የፈረንጆች ተወላጅ አቡነ አልፎንዝ መጣ፡፡ ከ 2 ዓመት በኋላም ንጉሱ የፈረንጆቹን
ሃይማኖት ስለተቀበለ በኢትዮጵያ ትልቅ ስደት ሆነ፡፡ ይህን ሃይማኖት ያልተቀበለ በሙሉ ግን እጣው ስደት ሆነ፡፡