Ethiopia TV +

የቀጥታ ስርጭት, ፊልሞች እና ሙዚቃ

ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : ስለ ሕጋዊ የፈቃድ ጋብቻ

ይህ መንገድ ወደ አበሳ ይስባልና ሴት የሌላቸው ወንድ ብቻውን ይኖር ዘንድ እንደማይገባው አወኩ፡፡ ለፊተኞቹ ሴት ታስፈልጋቸዋለች እንጅ ወንድ ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም፣ እንደተባለው በሰሩት ወጥመዳቸው እንዳይጠመዱ ሰዎች ተፈጥሯቸውን ክደው ሊኖሩ አይገባቸውም፡፡ ጌታየ ሀብቱም የዘመኑን ክፋት ፈርቼ መሰልኩ እንጂ መነኩሴ አይደለሁም አልኩት፡፡ ለጌታየም ሂሩት የተባለች አንዲት ቤተሰብ ነበረች፡፡ ምግባረ መልካምና ልባም፣ ትዕግስተኛ እንጂ ደም ግባታም አይደለችም፡፡ ጌታየ ሀብቱም "ይህች ልጅ ሚስት እንድትሆነኝ ስጠኝ" አልኩት "እሺ ከእንግዲህ ባሪያህ እንጂ ባሪያየ አይደለችም፡፡" "ሚስቴ ካልሆነች በስተቀር ባሪያየ አይደለችም፡፡ ወንድና ሴት በጋብቻ በአንድ ስጋና በአንድ ንብረት ትክክል ናቸው እና ጌታና ባሪያ ልንላቸው አይገባም፡፡" ጌታየ ሀብቱ "አንተስ የእግዚያብሔር ሰው ነህና እንደ ፈቃድህ አድርግ" አለኝ፡፡ ያቺንም ልጅ ጠራናት፡፡ እኔም "ሚስቴ ልትሆኝ ትወጃለሽን" አልኳት "ጌታየ እንደፈቀደ" አለችኝ ፡፡ ጌታየ ሀብቱም "እኔስ እፈቅዳለሁ" አላት፡፡ 17 እርሷም "ከአንተ እሚበልጥ የት አገኛለሁ መልካም" አለችኝ፡፡ ጌታየ ሀብቱም "አባታችን ሆይ ባርከን አልነው፡፡" "እግዚያብሔር ይባርካችሁና ይጠብቃችሁ፡፡ ለረዥም ጊዜ ፍቅርና ጤና ይስጣችሁ፡፡ ክፉ ነገርን ከእናንተ አርቆ በዚህ አለም ጥሪት ጋር ልጆች ይስጣችሁ" አለን፡፡ "አሜን" አልን፡፡ ይህችም ሂሩት ሚስቴ ሆነችና በጣም ወደደችኝ፡፡ በጌታየ ሀብቱ ቤት የተናቀች ነበረችና፣ ቤተሰቦቹም ዘወትር ያሳዝኗት ስለነበሩ ዛሬ በጣም ተደሰተች፡፡ እኔም ስለወደደችኝ በተቻለኝ ሁሉ እንዳስደስታት በልቤ ወሰንኩ፡፡ እንደኛ ጋብቻ ከእግዚያብሔር የተባረከና በፍቅር የፀና ሌላ ጋብቻ እሚገኝ አይመስለኝም፡፡ ከአክሱም በሸሸሁ ጊዜ ከእኔ ጋር የወሰድኩት የቀረኝ ሁለት ወቄት ወርቅ ነበረኝ፡፡ በእጅ ፅህፈቴም ከብቶችና ፍየሎች ፣ ልብስም አፈራሁ፡፡ በጌታየ ሀብቱ ጎረቤትም ትንሽ ቤት ሰራሁ፡፡ ከዚያም ከሚስቴ ጋር በፍቅር ነበርኩ፡፡ እኔ እየፃፍኩ የጌታየን የሀብቱን ልጆች ሳስተምር እርሷም ቀንና ሌሊት ትፈትል ነበር፡፡ ጌታየ ሀብቱም ልጆቹን ስላስተማረኩለት በየወሩ አንድ እንስራ ጤፍ ይሰጠኝ ነበር፡፡ እንዲህ ብየም ከሚስቴ ጋር በፍቅርና በመልካም ኑሮ አራት አመት ኖርኩ፡፡ በ1631 ዓ.ም ጥቅምት 11 ሰኞ ቀን ወንድ ልጅ ወለደችና በልጃችን ተደሰትን፡፡ በፀጋ አባቴ በሆነው ሰምም ሀብተ እግዚያብሔር ብየ ሰየምኩት፡፡ ከሦስት ዓመት በኋላም አቡነ አልፎንዝ ወደ ሀገሩ ሄደ፡፡ ጠላቶቼም ሁሉ ተነሱ፡፡ ወዳጆቹ ከእርሱ ጋር ተሰደዱ፡፡ በዚያን ጊዜም የጥንት ትምህርት የሚያስተምሩ መምህራኖች በሀገር ሁሉ ተፈለጉ በአክሱም ያሉት ዘመዶቼም እንደቀድሞው በአክሱም ሆኝ ወደ ሊቅነቴ ተመልሼ መፅሃፍትን እንዳስተምር ፈለጉኝ፡፡ በአቡነ አልፎንዝ ጊዜ የነበረውን ስደት ፈርቼ የሸሸሁ ስለመሰላቸው ጠላቶችህ ጠፍተዋልና ወዳጆችህ ድነዋልና ወደ እኛ ተመለስ ብለው መልክተኞች ላኩብኝ፡፡ እኔም ጠላት የለኝም፡፡ ይህ የእግዚያብሔር ሰው ጌታየ ሀብቱና ልጆቹ ሚስቴም ካልሆኑ በቀር ወዳጅ የለኝም፡፡ ከቶም ልተዋቸው አልችልምና ለኔ ወደ እናንተ መመለስ አይሆንልኝም እናንተም በሰላም ኑሩ ብዮ መለስኳአው፡፡ ይህም ግብዝ ጠላቴ መጀመሪያ ወደ ንጉስ ሱስንዮስ ያሳጣኝ ጠላቴ ወልደ ዩሐንስ አቡነ አልፎንዝ ከሄደ በኋላ ወደ ግብፃዊያን ሃይማኖት ተመለሰ፡፡ ነገር ግን ለጊዜው የሚመቸው ካላሆነ በስተቀር ሃይማኖት የለውም፡፡ ነገስታት ግብዞችና ሸንጋዮችን ይወዳሉና በሽንገላው ብዛትም ወደ ንጉስ ፋሲለደስ ሄዶ ወዳጅ ሆነ፡፡ ወልደ ዩሐንስም እኔ በእንፍራንዝ አገር በሰላም እንዳለሁ ሰምቶ እንደገና እርሱ የፈረንጆች አስተማሪ ነበር፡፡ አሁንም ተሸሽጎ የፈረንጆችን ትምህርት ያስተምራል ብሎ ለእንፍራንዝ ሹም ነገረው፡፡ እኔም ስለ ሽንገላው በጣም አዘንኩ፡፡ መጀመሪያ ስለኔ የፈረንጆች ጠላት ነው ፣ በኋላም ወዳጃቸው ነው አለ፡፡ ባዘነ ልቤም እግዚያብሔር 18 የደላይን ከንፈሮች ይቁረጣቸው ብየ በመዝሙር ለእግዚያብሔር ብዙ ቀን ፀለይኩ እግዚያብሔርም ሰማኝ፡፡ ይህም ሰው በብዙዎቹ የደምቢያ አድባራት ላይ ተሾመ፡፡ ሰዎች ጠልተው ገደሉት ፡፡ እሬሳውም በቤት ወድቆ ተገኝ፡፡ ገዳዩም አልተገኝም፡፡ ሹመቱና ገንዘቡንም ባእድ ወረሰው፡፡  

ተዛማጅ ልጥፎች:

  • ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : ስለ አምላክ መኖር እና የሃይማኖት ልዩነት ከፀሎት በኋላም ስራ ስለሌለኝ ሁልጊዜ ስለሰዎች ክፋትና ሰዎች በእርሱ ስም ሲበድሉ፣ ወንድሞቻቸውን ጉዋደኖቻቸውን ሲያባርሩ እና ሲገድሉ ዝም በማለቱ ስለፈጣሪ ጥበብ አስብ ነበር፡፡ በዚህም ጊዜ ፈረንጆቹ አየሉ፡፡ ነገር ግን ያገሩ ሰዎችም ከነሱ የባሰ ክፋት ሰሩ እንጅ ፈረንጆቹ ብቻቸውን አልነበረም የከፉት፡፡ የካቶሊክ ሃይማኖት የተቀበሉት ኦርቶዶክሶች 3… ተጨማሪ ያንብቡ
  • ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : ስለ ባህሪያዊ ዕውቀት የፈጣሪ ፈቃድ ግን ለእግዚያብሔር ለፈጣሪ ስገድ ፣ ሰውንም ሁሉ እንደነፍስህ አፍቅር ይላል፡፡ ይህ በልቦናችን እውነት መሆኑ ይታወቃል፡፡ እንደገናም በልቦናችን እውነትነቱ የሚታወቅ ሌላ እውነት "ሊያደርጉብህ የማትፈልገውን በሰው አታድርግ፡፡ ላንተ ሊያደርጉልህ የምትፈልገውን አድርግላቸው" ይላል፡፡ የሰንበትን ማክበር የሚለው ካልሆነ በቀር አስሩ የኦሪት ት… ተጨማሪ ያንብቡ
  • ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : ስለ ሃይማኖቶች መለየት ሌላ ትልቅ ምርመራ አለ፡፡ ሰዎች ሁሉ በእግዚያብሔር ዘንድ ትክክል ናቸው፡፡ እርሱም አንድ ህዝብ ለሕይወት አንድ ህዝብ ለሞት አንድም ለምህረት አንድም ለኩነኔ አልፈጠረም፡፡ ይህም አድሎ በስራው ሁሉ ፃድቅ በሆነ በእግዚያብሔር ዘንድ እንደማይገኝ ልቦናችን ያስተምረናል፡፡ ሙሴ ግን አይሁድን ለብቻቸው እንዲያስተምራቸው ተላከ፡፡ ለሌሎች ሕዝቦች ፍርዱ አልተነ… ተጨማሪ ያንብቡ
  • ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : ስለ አምላክ ህግና ስለ ሰው ህግ እግዚያብሔር የገዛ ህዝቡን እንዲያስቷቸው ስለምን ዋሾ ሰዎችን ይተዋል ብዮ አሰብኩ፡፡ እግዚያብሔር ግን ለሁሉም ለእያንዳንዱ እውነትንና ሐሰትን እንዲያውቅ ልቦና ሰጥቶናል፡፡ እውነት ወይም ሐሰት እንደፈቃዱ የሚመርጥበት መምረጫም ሰጠው፡፡ እውነትን ብንወድ ለፍጥረት ሁሉ አስፈላጊና ተገቢ የሆነውን እርሱም እንድናይበት እግዚያብሔር በሰጠን ልቦናችን ውስጥ እ… ተጨማሪ ያንብቡ
  • የኢትዮጵያ ታሪክ በፕሮፌሰር ተክሴን ነጋሽ እና ፕሮፌሰር አለማ እሴቴ <p>አሳሽዎ አይደገፍም.</p> … ተጨማሪ ያንብቡ

ታዋቂ ልጥፎች

እኛ ተከታታይ ፊልሞችን እና በርካታ የተጨመረ ነጻ ይዘት ወይም የደንበኝነት ምዝገባን የሚያቀርብ ጣቢያ ነው, በእርግጥ በቀጥታ እና በቀጥታ ለመመልከት እና ጥራት ያላቸውን የጥራት ደረጃ ይዘት ለማቅረብ በምናደርጋቸው ጥረቶች እና በጥራት ላይ አናመክርም. የምንሰግበው ነጻ የዥረት አገልግሎት ከሚሰጠን በስተቀር, ተከታታይ ፊልሞችን እና ፊልሞችን ወደ ኮምፒውተርዎ ማውረድ ይችላሉ, ቆይተው ለማየት እንዲያደርጉዋቸው, ለምሳሌ የበይነመረብ ግንኙነት ከሌለዎት. በቀጥታ ወደ ፊልሞች ከመሄድ የተሻለ ይሆናል, ሁሌም አስር ኪሎ ግራም ለ 2 ሰዓታት ፊልም አንፈልግም ማለት ነው, ስለዚህ ጣቢያዎቻችን ለቀኝ እይታ እና ተከታታይ ፊልሞችን ያቀርባሉ, ይህም አንድ ጊዜ ጠቅ በማድረግ ይዘትዎን በጥሩ ጥራት ለመመልከት ያስችልዎታል. እንዲሁም በቴሌቪዥን ወይም በሌሎች የዥረት አገልግሎት ላይ ለሚደረግ ማንኛውም ምርመራ የተመረጠውን በይነመረብ በቀጥታ መመልከት ይመርጣል. አብዛኛዎቹ እነዚህ አገልግሎቶች የሚከፈልባቸው ወይም ጥራት የሌላቸው ናቸው. ጊዜን እና አላስፈላጊዎቹን ፍለጋዎች ለመቆጠብ, በጣም ደጋግመው ጣቢያውን እናምናለን, ስለዚህ አብዛኛዎቹ ፊልሞች እና ተከታታይ ፊልሞች ቅድመ እይታ ወደ መጀመሪያ ጣቢያችን ይሄድና ከሌሎች ጣቢያዎች በበለጠ ፍጥነት ይሻሻላሉ. ከተለቀቀው ፊልም ወይም ተከታታይ ጋር በጣቢያው ላይ በቋሚነት ለመመልከት ሁሉም ፊልሞች እና ተከታታይ ፊልም ቅድመ-ኮድ ውስጥ ይቀመጣሉ, ስለዚህ ስራዎን ለእርስዎ እየሠራን ስለሆነ በድር ላይ ትርጉሞችን መፈለግ የለብዎትም. የመስመር ላይ ፊልሞች እና ፊልሞች የእርስዎ አዲሱ ፊልም ነው.