በ1625 ዓ/ም ሱስንዮስ ሞቶ ልጁ ፋሲለደስ ነገሰ፡፡ እርሱም በመጀመሪያ ፈረንጆቹን ወደደ፡፡ ግብፃዊያንንም አላባረራቸውም
በዚህ ምክንያት በኢትዮጵያ ሁሉ ሰላም ሆነ፡፡ የዚያን ጊዜ ከዋሻየ ወጥቼ መጀመሪያ ወደ አማራ አገሮች ሄድኩ፡፡ ኋላም ወደ
በጌምድር ተመለስኩ ለሁሉም በፈረንጆች ጠላትነት በሱስንዮስ ዘመን ከተባረሩት መነኮሳት አንዱ መሰልኳቸው ፡፡ ስለዚህም
ወደዱኝና ምግብና ልብስም ሰጡኝ፡፡ በዚህ ሁኔታ ከአገር ወደ አገር ስመላለስ የካህናቶቿን ክፋት አውቃለሁና ወደ አክሱም
መመለስን አልወደድኩም፡፡ ሰው የሚሄድበት ከእግዚያብሔር እንደሚታዘዝ አሰብኩ፡፡ ጌታ ሆይ የምሄድበትን መንገድና
የምኖርበትን ነገር ምራኝ አልኩት፡፡ ወደጎጃም ምድር ተሻግሬም ለመኖር አሰብኩ፣ ነገር ግን እግዚያብሔር ወደአላሰብኩት
መራኝ፡፡ አንድ ቀን ወደ እንፍራንዝ አገር ወደ አንድ ጌታ ሰው የእግዚያብሔር ሀብት ነውና ሀብቱ ወደ ተባለ ደረስኩ
በዚያውም አንድ ቀን አደርኩ፡፡ በማግስቱም አክሱም ወዳሉት ዘመዶቼ ደብዳቤ እንድልክ ከእርሱ ቀለምና ወረቀት
ለመንኩት፡፡ ይህ ሰውም
"አንተ ፀሀፊ ነህ ወይ?" አለኝ
"አዎ ፀሀፊ ነኝ" አልኩት
"ከኔ ጋር ጥቂት ቀን ተቀምጠህ የዳዊት መዝሙርን ፃፍልኝና ዋጋህን እሰጥሀለሁ" ብሎ ተናገረኝ
"እሺ" አልኩት፡፡
የድካሜንም ፍሬ የምመገብበትን መንገድ ስላሳየኝ እግዚያብሔርን በልቤ አመሰገንኩት፡፡ እውነት ባስተምር ሰዎች ሊጠሉኝና
ሊከሱኝ፣ ሊያባርሩኝ ካልሆነ አይሰሙኝምና ወደ ቀድሞ ሊቅነቴ ተመልሼ ሐሰትን ማስተማር ጠላሁ፡፡ እኔ ግን ከሰው ሁሉ
ጋር በፍቅርና በሰላም መኖርን ወደድኩ፡፡ በሃጥአን ቤት ከብሬ ከምኖር ግን ከሰው ተለይቼ የድካሜን ፍሬ እየተመገብኩ
እግዚያብሔር በሰጠኝ ጥበብ ተሸሽጌ አልባሌ መስየ መኖርን መረጥኩ፡፡ በጥቂት ጊዜም ቀለምና ብራና አዘጋጅቼ አንድ
16
የዳዊት መዝሙር ፃፍኩ፡፡ ፅህፈቴም ያማረች ናትና ጌታዮ ሀብቱና ሁሉም አይተዋት ተደነቁ፡፡ ጌታዮ ሀብቱም ደሞዜን አንድ
መልካም ልብስ ሰጠኝ ፤ ደግሞም ወልደ ሚካኤል የተባለ የጌታየ ሀብቱ ልጅ ላባቴ እንደፃፍከው ለእኔም ፃፍልኝ አለኝና
ፃፍኩለት፡፡ አንድ በሬና ሁለት ፍየሎችም ሰጠኝ፡፡ ከዚህ በኋላ ብዙዎች ወደ እኔ ዘንድ መጥተው ዳዊትና ሌሎች
መፅሐፍትን፣ ደብዳቤዎችን አፃፉ፡፡ በዚያ አገር ካለ እኔ በቀር ሌላ ፀሐፊ አልነበረምና ልብስ፣ ፍየሎች፣ እህል፣ ጨውና
ሌላም እነርሱን የመሳሰሉ ሰጡኝ፡፡ ለጌታየ ሀብቱም አንድ ወልደ ገብርኤል ተሰማ የተባለና ሁለተኛ ወልደ ህይወት ምትኩ
የተባሉ ሁለት ልጆች ነበሩት፡፡ አባታቸው ሀብቱም የሚበቃህን ምግብ እሰጥሃለሁና በእጅህ ፅፈህ የምታፈራውን ላንተ
ይሆናልና፤ የዳዊትን ንባብ አስተምራቸው አለኝ፡፡ አባቴ ሆይ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ አልኩት፡፡ ነገር ግን ካንተ በቀር
ዘመድ የለኝምና በአባቴና በእናቴ ዘመዶችም ፋንታ ዘመድ ሁነኝ አልኩት፡፡