የፈጣሪ ፈቃድ ግን ለእግዚያብሔር ለፈጣሪ ስገድ ፣ ሰውንም ሁሉ እንደነፍስህ አፍቅር ይላል፡፡ ይህ በልቦናችን እውነት
መሆኑ ይታወቃል፡፡ እንደገናም በልቦናችን እውነትነቱ የሚታወቅ ሌላ እውነት "ሊያደርጉብህ የማትፈልገውን በሰው
አታድርግ፡፡ ላንተ ሊያደርጉልህ የምትፈልገውን አድርግላቸው" ይላል፡፡ የሰንበትን ማክበር የሚለው ካልሆነ በቀር አስሩ
የኦሪት ትዕዛዛት የፈጣሪ ናቸው፡፡ ሰንበትን ለማክበር ግን ልቦናችን ዝም ይላል፡፡ ልንገድልና ልንሰርቅ፣ ልንዋሽና የሰው
ሚስት ልንሰርቅ ይህን የሚመስለውን ልናደርግ እንደማይገባን ልቦናችን ይነግረናል፡፡ እንዲሁ ስድስቱ የወንጌል ቃላት
የፈጣሪ ፈቃዶች ናቸው፡፡ እኛ ይህን የምህረት ስራ ሊያደርጉልን እንፈልጋለን፡፡ በሚቻለን ለሌሎች ልናደርግላቸው
ይገባናል፡፡ ደግሞም በዚህ ዓለም ሕይወታችን፣ ንብረታችን እንድንጠብቅ የፈጣሪ ፈቃድ ነው፡፡ ከፈጣሪ ፈቃድ ወጥተን
በዚህ ሕይወት እንኖራለን፡፡ በተቀደሰ ፈቃዱ ካልሆነ በቀር ልንተወው አይገባንም፡፡ እርሱ ፈጣሪያችን ለሁሉ ልቦናና ችሎታ
ስለሰጠ ኑሯችንን በዕውቀትና በሥራ እንድናሳምረው ይፈቅድልናል፡፡ ይህ ካልሆነ በቀር የሕይወታችን ፍላጎት አይገኝም፡፡
እንዲሁ አንዱ ካንዷ ጋር መጋባትና ልጆች ማሳደግን ፈቅዷል፡፡ ደግሞም ከልቦናችን ጋር የሚስማማ ለህይወታችንም
ለሁሉም የሰው ልጆች ኑሮ የሚያስፈልጉ ሌሎች ብዙ ሥራዎች አሉና የፈጣሪ ፈቃድም እንዲሁ ስለሆነ ልንጠብቀው
ይገባናል፡፡ እግዚያብሔር ፍፁማን አድርጎ እንዳልፈጠረን ልናውቅ ይገባናል፡፡ ለመፈፀማችን የተዘጋጀን አዋቂዎችና በዚህም
ዓለም እስካለን ድረስ እንድንፈፅምና ፈጣሪያችን በጥበቡ ላዘጋጀልን ዋጋ የተዘጋጀን እንድንሆን አድርጎ ፈጠረን፡፡ በዚህ
ምድር ፍፁማንና ብፁዓን አድርጎ ሊፈጥረን ለእግዚያብሔር ይቻለው ነበር፡፡ ነገር ግን ለመፈፀማችን እምንዘጋጅ አድርጎ
ፈጠረን እንጅ እንዲሁ ሊፈጥረን አልፈቀደም፡፡ ከሞታችን በኋላ ፈጣሪያችን ለሚሰጠን ዋጋ የተዘጋጀን ፍፁማን እንድንሆን
በዚህ የፈተና ዓለም መካከል አኖረን፡፡ በዚህ ዓለም እስካለንም ወደ እርሱ እስኪወስደን ድረስ እየታገስን ፈቃዱን እየፈፀምን
ፈጣሪያችን ልናመሰግነው ይገባል፡፡ የፈተናችንንም ጊዜያቶች እንዲያቀልልን ባለማወቃችን ሠራነውን የእብደት አበሳ
እንዲተውልን የተፈጥሮ ሕግጋትን አውቀን እንድንጠብቃቸው ልቦና እንዲሰጠን ወደቸርነቱ እንለምን፡፡ ፀሎት ደግሞ ላዋቂ
ነፍስ አስፈላጊ ነውና ዘወትር ልንፀልይ ይገባናል፡፡ አዋቂ ነፍስ ሁሉን የሚያውቅና ሁሉን የሚጠብቅ ሁሉን የሚገዛ
እግዚያብሔር እንዳለ ታውቃለች፡፡ ወደ እርሱ እንድትፀልይም ከእርሱ መልካም እንድትለምን፣ ከክፉ እንድትድንና ሁሉን
ወደ ሚችል እጅ እንድትማፀን ወደ እርሱ ትሳባለች፡፡ እግዚያብሔር ምሁርና ትልቅ ነው፡፡ የሚሳነውም የለም፡፡ ከበታቹ
ያለውን ያያል፣ ሁሉንም ይይዛል፣ ሁሉን ያውቃል ፣ ሁሉን ይመራል፣ ሁሉን ያስተምራል አባታችን ፈጣሪያችን ጠባቂያችን
ነው፡፡ የነፍሳችን ዋጋ ቸርና ይቅር ባይ ችግራችንን ሁሉ የሚያውቅ ነው፡፡ ለሕይወት እንጂ ለጥፋት አልፈጠረንም፡፡
በትዕግስታችን ይደሰታል፡፡
12
ጠቢቡ ሰለሞን
"ጌታ ሆይ አንተ ከሁሉ በላይና ቻይ ነህና ሁሉን ታስተምራለህ፣ ሰዎችን ለንስሃ ታቆያቸዋለህ፣ ሃጢያታቸውንም ችላ
ትለለህ፣ አንተም ያደረከውን ሁሉ ምንም የምትንቀው ስለማይኖር ሁሉን ትወዳለህ፡፡ በሁሉ ፍጥረት ላይም ትራራለህ ይቅር
ትላለህ" ይላል፡፡
የእግዚያብሔርም ታላቅነቱን እንድናስብ ለስጋችንና ለነፍሳችን እሚያስፈልገንን ለማግኝት ወደ እርሱ እንድንፀልይና
እንድናመሰግነው አዋቂዎች አድርጎ ፈጠረን፡፡ ይህም ሁሉ በሰው ልብ ያገባ ፈጣሪያችን ዕውቀት ያስተምራልና እንዴትስ
ሀሰት ሊሆን ይችላል፡፡